በማሊ ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ‘ሚናካ’ በተባለ ግዛት ውስጥ፣ ዛሬ ዓርብ በርካታ የማሊ ወታደሮች መገደላቸውን የሀገሪቱ ሠራዊት አስታውቋል። ጥቃቱ በጂሃድስት ተዋጊዎች የተፈጸመ ነው ሲል ሠራዊቱ ጨምሮ አስታውቋል።
የሠራዊቱ ቃል አቀባይ “በመጀመሪያው ቆጠራ ስድስት ሰዎችን አጥተናል” ያሉ ሲሆን “በህይወት የተረፉ ቀሪዎቹን ወታደሮች ማፈላለጉ ቀጥሏል” ብለዋል፡፡
“አሸባሪዎቹ ቢያንስ 15 ተዋጊዎቻቸውን አጥተዋል” ሲሉም ቃል አቀባዩ አክለዋል፡፡
የሐሙሱን ጥቃት ተከትሎ፣ እስከ 20 የሚደርሱ ሰዎች ተጎድተዋል ወይም ተሰውረዋል ሲሉ አንድ አካባቢው ባለሥልጣን ተናግረዋል፡፡
ጥቃቱ የተፈጸመው ወደ አጎራባች ኒዤር ይጓዙ የነበሩትን የጭነት ተሽከርካሪዎች ሲያጅብ በነበረ አንድ የሠራዊቱ ክፍል ላይ በደረሰ ደፈጣ መሆኑን ባለስልጣኑ አክለው ገልጸዋል፡፡ ኒዤር ባለፈው ሳምንት የመንፈቅለ መንግሥት የተካሄባት ሲሆን፣ ክስተቱን ተከትሎ ከጎረቤት አገሮች ጋር መፋጣጧ ተነግሯል፡፡
የኒዤር ጉዳይ በአካባቢው ቀውስ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ስለመሆኑም የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል፡፡
መድረክ / ፎረም