በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ሁለት የዩክሬን ድሮኖች የባህር ኃይል ጦር ሠፈሬን ለማጥቃት ሞክረዋል” - ሩሲያ


ዐርብ ነሐሴ 4፣ 2023 ከተለቀቀ ቪዲዮ ላይ የተነሳው ይህ ፎቶ፣ በጥቁር ባህር በሚገኘው የኖቮሮሲስክ ወደብ አቅራቢያ፣ ንብረትነቱ የሩሲያ ነው በተባለ ትልቅ መርከብ ላይ ድሮን ሲያንዣብብ ያመለክታል።
ዐርብ ነሐሴ 4፣ 2023 ከተለቀቀ ቪዲዮ ላይ የተነሳው ይህ ፎቶ፣ በጥቁር ባህር በሚገኘው የኖቮሮሲስክ ወደብ አቅራቢያ፣ ንብረትነቱ የሩሲያ ነው በተባለ ትልቅ መርከብ ላይ ድሮን ሲያንዣብብ ያመለክታል።

ሩሲያ፤ ሁለት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ትናንት ሌሊቱን ‘ኖቮሮሲይስክ’ የተባለውንና የጥቁር ባህር ላይ የሚገኘውን ባህር ሃይል ጦር ሰፈሯን ለማጥቃት ሞክረዋል ስትል ዛሬ ዓርብ አስታወቃለች፡፡

በጥቃቱ የሩሲያ የጦር መርከቦች ክፉኛ ተጎድተዋል ሲሉ ሁለት ምንጮች ለሮይተርስ መናገራቸውም ተዘግቧል፡፡

እህል ወደ ውጭ የሚላክበት እና 2 ከመቶ የዓለም የነዳጅ አቅርቦቶችን የሚያስተናግደው የሲቪል ወደብ፣ የመርከብ እንቅስቃሴዎችን ለጊዜው ማቆም ነበረበት ሲል፣ በቦታው የካስፔያንን ነዳጅ ጣቢያ የሚቆጣጠረው የንግድ ማህበር አስታውቋል።

ሩሲያ ሁለት የሰው አልባ አውሮፕላኖች ተደምስሰዋስል ስትል አስታውቃለጭ

በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት፣ የሩሲያ የንግድ ወደብ ዒላማ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዩክሬንና አጋሮችዋ፣ በዚህ ሳምንት መገባደጃ ሳዑዲ አረቢያ በምታስተናግደው የሰላም እቅድ ውይይት ላይ ዓለም አቀፍ ድጋፋ ለማሰባሰብ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

በሳውዲ አረቢያ የወደብ ከተማ ጀዳ በሚካሄደው ስብሰባ፣ ማንኛውም የሰላም ዕቅድ፣ በዩክሬን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት እንዲያበቃ የሚያደርግ እንዲሆን እና፣ ቁልፍ በሆኑ መርሆዎች ላይ የዩክሬን እና የምዕራባውያን ዲፕሎማቶች እንዲስማሙ ዕድል ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በስብሰባው ላይ ወደ 40 የሚጠጉ ሀገራት እንዲወከሉ ዝግጅት ቢኖርም ቻይና ከእነዚህ መካከል ስለመገኘቷ ግልጽ አይደለም፡፡

ቻይና ከዚህ ቀደም ብሎ በሰኔ ወር ዴንማርክ ላይ በተካሄደው የውይይት መድረክ እንድትገኝ የተጋበዘች ቢሆንም ሳትገኝ ቀርታለች፡፡

በጀዳ የታቀደው ስብሰባ ዛሬ ዓርብ ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ዋነኛው ንግግር የሚካሄደው ቅዳሜ እና እሁድ መሆኑ

ተመልክቷል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለነስኪ ቅዳሜ እና እሁድ የሚካሄደው ንግግር በመጭው መጸው ወደ ሚደረገው ትልቁ የዓለም ሰላም ጉባኤ ይመራል ብለው ተስፋ ማድረጋቸውን ከትናንት በስቲያ ረቡዕ አስታውቀዋል።

ሩሲያ፤ ከዛሬ ጀምሮ ቅዳሜና እሁድ ይካሄዳል በተባለው ንግግር ወይም ዜለነስኪ በመጭው መጸው ይደረጋል ብለው ባቀዱት ጉባኤ እንደማትሳተፍ ተገልጿል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG