በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፌዴራል መንግሥት በዐማራ ክልል የጸጥታ መደፍረስ ጣልቃ እንዲገባ ርእሰ መስተዳድሩ ጠየቁ


የፌዴራል መንግሥት በዐማራ ክልል የጸጥታ መደፍረስ ጣልቃ እንዲገባ ርእሰ መስተዳድሩ ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:59 0:00

በዐማራ ክልል የተከሠተውን የጸጥታ መደፍረስ ለመቆጣጠር፣ ለክልሉ አዳጋች እንደኾነ የገለጸው የርእሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት፣ የፌዴራል መንግሥቱ፣ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ጣልቃ ገብቶ ተገቢውን ርምጃ እንዲወስድ ጠየቀ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በክልሉ ፕሬዚዳንት ዶር. ይልቃል ከፋለ የተፈረመውንና በአድራሻ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት የተጻፈውን ደብዳቤ አያይዞ ባወጣው ዘገባ፣ ፌዴራል መንግሥቱ፣ በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት፣ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስድ ክልሉ መጠየቁን አስታውቋል።

ርእሰ መስተዳድሩ በዚኹ ደብዳቤያቸው፣ በክልሉ የተከሠተው የሰላም መደፍረስ፣ ከፍተኛ ሰብአዊ፤ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እያስከተለ እንደሚገኝ ጠቅሰው፣ ኹኔታውን በመደበኛ የሕግ ማስከበር ሥርዐት ለመቆጣጠር አዳጋች በመኾኑ፣ የፌዴራል መንግሥቱ፣ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ተገቢውን ርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

የክልሉ ፕሬዚዳንት፣ ትላንት በአሚኮ በተላለፈው መግለጫቸው፣ በክልሉ እየተስፋፋ የመጣው የጸጥታ መደፍረስ እና ትንኮሳ፣ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ መኾኑን ጠቅሰው፣ ኹለንተናዊ ቀውስ ከማድረሱ በፊት፣ በሰላማዊ ውይይት እና ምክክር እንዲፈታ ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG