በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጉራጌ ዞን የመስቃንና ማረቆ ወረዳዎች አካባቢ ግጭት መረጋጋቱን ፖሊስ አስታወቀ


በጉራጌ ዞን የመስቃንና ማረቆ ወረዳዎች አካባቢ ግጭት መረጋጋቱን ፖሊስ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:33 0:00

የሰላማዊ ሰዎችን ግድያ ተከትሎ፣ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በመስቃንና ማረቆ ወረዳዎች አካባቢ፣ ዳግም የተቀስቀሰውን የጸጥታ ሁከት እና ግጭት፣ የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ ፖሊስ ማረጋጋቱን፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ዓለማየሁ ማሞ አስታወቁ።

በምሥራቅ መስቃን፣ ሰሜን ዲዳ በምትባል ቀበሌ፣ ወደ ገበያ በማቅናት ላይ የነበሩ ሰባት ሰዎች እንደተገደሉ፣ ፖሊስ ማረጋገጡን ገልጸዋል።

ነዋሪዎች፣ አካባቢው እንደተረጋጋ እና ወደ አንጻራዊ ሰላም እንደተመለሰ ተናግረው፣ ዳሩ ግን ወንጀለኞቹ ባለመያዛቸው፣ የደኅንነት ስጋት እንደሚሰማቸው ተናግረዋል።

ከሰኔ 25 ቀን እስካለፈው ቅዳሜ ሐምሌ 22 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ፣ 20 ሰዎች እንደተገደሉ፣ የምሥራቅ መስቃን ወረዳ ፖሊስ፣ ለአሜሪካ ድምፅ መግለጹ አይዘነጋም።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG