በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ዕዳ


 የኢትዮጵያ ዕዳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:02 0:00

ኢትዮጵያ የስድሣ ቢሊየን ስድስት መቶ ሚሊየን ዶላር ጥሬ ብድርና ወለድ አጠቃላይ ዕዳ እንዳለባት የገንዘብ ሚኒስቴሯ ሰሞኑን አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለፓርላማው በቅርቡ በሰጡት ማብራርያ መንግሥታቸው የሃገሪቱን ዕዳ ከነበረበት የ59 ከመቶ የአጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት ንፅፅር ወደ 38 ከመቶ ዝቅ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

ከአጠቃላዩ የሃገር ውስጥ ምርት አንፃር ሲታይ ዕዳው ብዙ መስሎ ባይታይም ከሃገሪቱ የመክፈል አቅም አንፃር ሲለካ ግን ከፍተኛ መሆኑን የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶክተር ጉቱ ቴሶ ተናግረዋል።

ሌላው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ዶክተር ኢዮብ ተስፋዬ ደግሞ መንግሥት አጠቃላይ የልዕለ ምጣኔ ኃብት መፍትኄ ሊያስገኙ በሚችሉ እርምጃዎች ላይ እንዲያተኩር ይመክራሉ።

በሌላ በኩል የዓለም ባንክ ቡድን ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ ኢትዮጵያ ጉብኝት ላይ ናቸው። ባንኩም ሰሞኑን የ400 ሚሊየን ዶላር የእርዳታና ብድር ስምምነት ይፋ አድርጓል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያገኛሉ፡፡

XS
SM
MD
LG