በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመተማ ወረዳ ከሳምንታት በፊት በታጣቂዎች የታገቱ ስድስት ሰዎች እንደተገደሉ ተሰማ


በመተማ ወረዳ ከሳምንታት በፊት በታጣቂዎች የታገቱ ስድስት ሰዎች እንደተገደሉ ተሰማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:22 0:00

በዐማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ ከመሸላ በተባለ ቀበሌ፣ ከሦስት ሳምንት በፊት፣ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ ስድስት ግለሰቦች መገደላቸውን፣ ቤተሰቦቻቸው አረጋገጡ፡፡

በሌላ በኩል፣ በዚኹ በመተማ ወረዳ፣ የዳስ ጉንዶ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አከለ መለሰ፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ከሳምንት በፊት፣ ታጣቂዎች፣ በቀበሌው የእርሻ ሥራቸውን እያከናወኑ በነበሩ አርሶ አደሮች ላይ የግድያ እና የእገታ ድርጊት ፈጽመዋል፡፡

ለታጋች ቤተሰቦችም ስልክ ደውለው፣ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠር የማስለቀቂያ ገንዘብ እንዲከፍሉ እንደጠየቋቸው፣ የቤተሰቦቻቸው አባላት ተናግረዋል፡፡ የቀበሌው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አከለ መለሰ፣ ለግድያ እና ለእገታ አድራጎቱ፥ በጫካ የነበሩና በእርቀ ሰላም ስም ተመልሰው ወደ ማኅበረሰቡ የተቀላቀሉትን፣ “ጽንፈኛ” ሲሉ የጠሯቸውን፣ የቅማንት ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቄ፣ ከሦስት ሳምንታት በፊት፣ በተጠቀሱት የወረዳው አካባቢዎች፣ ግድያ እና እገታ መፈጸሙን አምነው፣ በአካባቢው ታጥቀው በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ላይ ርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ዝርዝርን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG