በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሸዋ ሮቢትና ወልዲያ ውስጥ ሲቪሎች በተኩሶች ተገድለዋል


ሸዋ ሮቢትና ወልዲያ ውስጥ ሲቪሎች በተኩሶች ተገድለዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:21 0:00

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋ ሮቢትና ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተሞች ውስጥ በተከፈቱ ተኩሶች ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ሸዋ ሮቢት ውስጥ ተገደሉ ስለተባሉት ሰዎች ማንነትና ብዛት ከአካባቢው ባለሥልጣናትና ከጤና ተቋማት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ያደረነው ጥረት አልተሳካም።

በተያያዘ ዜና በሰሜን ወሎ ዞን የጉባላፍቶ ወረዳ ትምህርት ፅህፈት ቤት ኃላፊን “ማንነታቸው ያልታወቀ ሰዎች ትላንት ምሽት ተኩሰው ገድለዋቸዋል” ሲሉ የከተማዪቱ ነዋሪዎች ቢገልፁም የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ግን የባለሥልጣኑን ህልፈተ ህይወት አረጋግጦ መንስዔውን ሳይገልፅ ቀርቷል። ቢያረጋግጥም መንሥኤውን አልገለጸም፡፡

ዝርዝርን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG