በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ተጨማሪ ክስ ቀረበባቸው


ዶናልድ ትረምፕ (ፎቶ ፋይል ኤኤፍፒ)
ዶናልድ ትረምፕ (ፎቶ ፋይል ኤኤፍፒ)

የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ባለባቸው 37 ዝርዝር ክሶች ላይ ሶስት ተጨማሪ ክሶች ባለፈው ሐሙስ እንደቀረበባቸው ታውቋል።

አሜሪካ ኢራን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ያወጣችው ሚስጥራዊ ወታደራዊ ሰነድን በሕገ ወጥ መንገድ ይዘዋል የሚል አንድ ክስ፣ እንዲሁም ሁለት ክሶች ደግሞ፣ የወሰዷቸውን ሚስጥራዊ ሰነዶች በተመለከተ በሚደረገው ምርመራ ወቅት፣ ሰነዶቹን “ለመደበቅ፣ ለመቀየር፣ ለማጥፋት ወይም ለመቅደድ” ሞክረዋል የሚሉ ናቸው።

አዲሶቹ ክሶች ከትረምፕ በተጨማሪ፣ ፍሎሪዳ በሚገኘው ማር አ ላጎ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ይሠራ በነበረ ግልሰብም ላይ መመሥረቱ ታውቋል።

ትረምፕ ሰነዶቹን እንዲመልሱ በተደጋጋሚ ተጠይቀው እንደነበር በክሱ ላይ ተመልክቷል።

በተጨማሪም ትረምፕ እና ረዳቶቻቸው በማር አ ላጎ መኖሪያ ቤታቸው የሚገኝ የደህንነት ካሜራ የያዛቸውን ቅጂዎች እንዲሠርዝ አንድ የቤቱን ሠራተኛ ጠይቀዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

አሜሪካ ኢራን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ያወጣችው ሚስጥራዊ ወታደራዊ ሰነድን ለአንድ ጽሃፊ፣ ለአንድ አሳታሚ እና ሁለት ረዳቶቻቸው ከሁለት ዓመታት በፊት ኒው ጀርሲ በሚገኝ የጎልፍ ክለባቸው ውስጥ አሳይተዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

ትረምፕ በተጨማሪም በአሜሪካ የተደረገውን የ2020 ምርጫ ውጤት ለመቀልበስ እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግርን ለማስቆም በኮንግረስ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ላይ ያላቸውን ሚና በተመለከት ክስ ይጠብቃቸዋል።

ጥፋተኛ የሚባሉ ከሆነ ሁከት ሊከተል እና ሀገሪቱንም ሊበታትን ይችላል ሲሉ ትረምፕ ያስጠነቅቃሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG