በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሃምዳን ዳጋሎ ሠራዊቱ አል ቡርሃንን ይዞ እንዲያስረክብ ጥሪ አደረጉ


ጄነራል ሃምዳን ዳጋሎ (ፎቶ ፋይል AP)
ጄነራል ሃምዳን ዳጋሎ (ፎቶ ፋይል AP)

በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሪ የሆኑት ጄኔራል ሞሃመድ ሃምዳን ደጋሎ፣ “የሱዳን ሠራዊት ዓባላት፣ ተቀናቃናቃኛቸው የሆኑትን የሠራዊቱ አዛዥ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃንን እና ሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችን ይዘው ካስረከቡ፣ ጦርነቱ በ72 ሰዓታት ውስጥ ቆሞ፣ ሰላም ሊመለስ ይችላል” ሲሉ፣ መናገራቸው ተሰምቷል።

ጦርነቱ ከጀመረ አንስቶ የመጀመሪያው ነው በተባለና፣ ወታደራዊ ልብስ ለብሰውና በወታደሮቻቸው ታጅበው ትናንት ዓርብ በለቀቁት የ 5 ሰቂቃ የቪዲዮ መልዕክት፣ ወደ ሠላም ለመመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው ሃምዳን ዳጋሎ ተናግረዋል።

ጦርነቱ ትናንት ዓርብም ቢሆን መቀዛቀዝ አላሳየም ነበር። ሕዝብ በብዛት በሚኖርባቸው የመዲናዋ ካርቱም መንደሮች የአየር እና የሮኬት ጥቃቶች ደርሰው እንደነበር የኤኤፍፒ ዜና ወኪል ነዋሪዎችን ጠቅሶ ዘግቧል።

ያርሙክ በተሰኘው የመሣሪያ ማምረቻ እና ማከማቻ ላይ ፍንዳታ እንደነበር የዓይን እማኞች መናገራቸውን ሪፖርቱ ጨምሮ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG