በናይሮቢ የሚኖሩ በርካታ ስደተኞች፣ ኬንያውያን በስፋት የሚግባቡባቸውን ሁለቱን ቋንቋዎች፣ እንግሊዘኛንም ኾነ ስዋሂሊን፣ አጥርተው አይናገሩም።
ይኸው የቋንቋ ተግባቦት ውስንነት፣ ስደተኞች፣ ከኅብረተሰቡ ጋራ ለመዋሐድ ጥረት በሚያደርጉት ወቅት፣ ብርቱ እክል ይጋርጥባቸዋል።
ኹኔታውን ለመቀየር እየተደረገ ስላለው የአንድ ዩኒቨርሲቲ ጥረት፣ ሁባህ አብዲ ከናይሮቢ ያጠናቀረችውን ዘገባ ዝርዝር፣ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።