በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሸገር ከተማ አስተዳደር ለቤት ፈረሳ አቤቱታዎች እንዲመልስ የጊዜ ገደብ ተሰጠው


የሸገር ከተማ አስተዳደር ለቤት ፈረሳ አቤቱታዎች እንዲመልስ የጊዜ ገደብ ተሰጠው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:21 0:00

- “በጊዜ ገደቡ ምላሽ ካልሰጠ ወደ ክሥ እናመራለን”- የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም

የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ ቤቶቻቸው ለፈረሱባቸው ሰዎች አቤቱታዎች፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር ምላሽ እንዲሰጥ መጠየቁን አስታወቀ፡፡

ተቋሙ፣ ከሸገር ከተማ አስተዳደር የቤቶች ፈረሳ ጋራ ተያይዞ፣ ከ100 ሺሕ በላይ አቤቱታዎችን እንደተቀበለ፣ ከዚኽ ቀደም ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምርመራ ዲሬክተር አቶ ቶሌራ በላይ፣ የከተማ አስተዳደሩ፥ ለአቤቱታዎቹ ምላሽ እንዲሰጥ በደብዳቤ እንደተጠየቀ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

የሸገር ከተማ አስተዳደር፣ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ምላሽ የማይሰጥ ከኾነ፣ ጉዳዩ ወደ ክሥ እንደሚያመራ፣ የምርመራ ዲሬክተሩ አቶ ቶሌራ በላይ አመልክተዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ከሸገር ከተማ አስተዳደር አስተያየት ማግኘት አልቻልንም፡፡ ይኹንና፣ አስተዳደሩ ቀደም ሲል በሰጠው ምላሽ፣ “ለእንባ ጠባቂ ተቋም 100 ሺሕ አቤቱታዎች መቅረባቸውን አላውቅም፤” ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ በሸገር ከተማ፣ “ሕገ ወጥ ግንባታ” በሚል እየተካሔደ ካለው የቤቶች ፈረሳ ጋራ የተያያዙ፣ 100 ሺሕ አቤቱታዎችን እንደተቀበለ፣ ቀደም ሲል ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል፡፡ አሁን ደግሞ፣ እንባ ጠባቂ ተቋሙ፥ የሸገር ከተማ አስተዳደር ለአቤቱታ አቅራቢዎቹ ምላሽ እንዲሰጥ፣ የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ እንደጠየቀው አስታውቋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ከሸገር ከተማ አስተዳደር ሐላፊዎች፣ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት፣ ለዛሬ አልተሳካም፡፡ ኾኖም፣ የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጉግሳ ደጀኔ፣ ቀደም ሲል ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ ከቤቶች ፈረሳ ጋራ ተያይዞ፣ 100 ሺሕ ቅሬታዎች መቅረባቸውን አናውቅም፤ ብለዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG