በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ “የትምህርት ክፍሎች ይዘጋሉ” የሚለውን የመምህራን ስጋት አስተባበለ


 የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ “የትምህርት ክፍሎች ይዘጋሉ” የሚለውን የመምህራን ስጋት አስተባበለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:50 0:00

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሥር በሚገኙ አራት ኮሌጆች ውስጥ ያሉ 18 የትምህርት ክፍሎች እንዲዘጉ መወሰኑን፣ የዩኒቨርሲቲው መምህራን ማኅበር አስታወቀ፡፡

የዐማርኛ ቋንቋን ጨምሮ የሌሎች ትምህርት ክፍሎችን መዘጋት የተቃወመው የዐማራ ክልል የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማኅበርም፣ “ውሳኔው፥ ፖለቲካዊ ተጽእኖ ያለበት ነው፤” ብሏል፡፡

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በበከሉ፣ “መረጃው ከእውነት የራቀ ነው፤” ሲል አስተባብሏል፡፡

ዩኒቨርሲቲው፣ እንደ ሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው አቅጣጫ፣ የተልእኮ እና የትኩረት መስክ ለይቶ እየተንቀሳቀሰ እንደኾነ ጠቅሷል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው፣ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣ በተልእኮ እና በትኩረት መስክ ልየታው መሠረት፣ ከነበረበት የመውጫ ስትራቴጂ ነድፎ እንቅስቃሴ መጀመሩ፣ ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም አርኣያ ያደርገዋል፤ ብለዋል፡፡

/የዘገባውን ሙሉ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG