የአፍሪካ መሪዎች፣ ከሁለተኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ እና የኢኮኖሚ ፎረም አስቀድመው፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ቅዱስ ፒተርስበርግ መግባት እንደ ጀመሩ ተነገረ፡፡
የምግብ ደኅንነት እና የቫግነር ወታደራዊ ቡድን የወደፊት ዕጣ፣ የጉባኤው ከፍተኛ አጀንዳ ይኾናል፤ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል፡፡
የፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን መንግሥት፣ በዓለም አቀፉ መድረክ ተሰሚነቱ እየጨመረ ለመጣውና 1ነጥብ3 ቢሊዮን ለሚደርሰው፣ የአፍሪካ አህጉር ሕዝብ ወዳጅነት ያለውን ቁርጠኝነት ማሳየት ይኖርበታል፤ ተብሏል፡፡
ለሩሲያ ጥሩ አቀባባል ከሚያሳየው የዓለም ክፍልም፣ አገሪቱ ተጨማሪ አጋሮችን እንደምትሻ ተገልጿል፡፡
የአፍሪካ መሪዎች ልኡካን ቡድን፣ በሩሲያ - ዩክሬኑ ጦርነት ሰላም እንዲመጣ፣ ባለፈው የተጓዙበትን የማደራደር ውጥን፣ በድጋሚ ሊሞክሩት ይችላሉ፤ የሚል ግምት መኖሩም ተመልክቷል፡፡
መድረክ / ፎረም