በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ስምንት ባለልዩ ተልዕኮ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚኖሯት ተገለጸ


ኢትዮጵያ ስምንት ባለልዩ ተልዕኮ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚኖሯት ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:39 0:00

ኢትዮጵያ ስምንት ባለልዩ ተልዕኮ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚኖሯት ተገለጸ

በኢትዮጵያ፣ ከመጪው ዓመት ጀምሮ፣ ስምንት ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር ተቋም ኾነው እንደሚደራጁ፣ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መልሶ ማደራጀት ጉዳይ መግለጫ የሰጡት፣ የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ዶር. ሳሙኤል ክፍሌ፣ እስከ አሁን ድረስ፣ ኹሉም ዩኒቨርሲቲዎች አጠቃላይ ትምህርት ሲሰጡ የቆዩበት ሥርዐት ውጤታማ ሊያደርጋቸው እንዳልቻለ ተናግረዋል፡፡ ከእንግዲህ ተቋማቱን፣ በትኩረት እና በተልዕኮ በመለየት፣ መልሶ የማደራጀት ሥራ አስፈላጊ ኾኖ እንደተገኘ ገልጸዋል፡፡

በዚኽም መሠረት፣ በአገሪቱ የሚገኙ 47 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች፣ በአራት የትኩረት መስኮች እንደተለዩና በመጪው ዓመት በተለዩባቸው መስኮች ወደ ሥራ እንደሚገቡ አስታውቀዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡት፣ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚድያ እና ኮሙኒኬሽንስ መምህር ዶር. ጌታቸው ጥላሁን፣ ውሳኔው፥ ለአገሪቱ ጠቀሜታን የሚያስገኝ ቢኾንም፣ አተገባበሩ ግን ጥንቃቄ ያስፈልገዋል፤ ብለዋል፡፡ ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG