በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፋር እና በዐማራ ክልሎች በሳምንት ውስጥ ሦስት የረድኤት ሠራተኞች እንደተገደሉ ተገለጸ

አፋር እና በዐማራ ክልሎች በሳምንት ውስጥ ሦስት የረድኤት ሠራተኞች እንደተገደሉ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:47 0:00

ባለፈው የአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ፣ በአፋር እና ዐማራ ክልሎች፣ ሦስት የረድኤት ሠራተኞች እንደተገደሉ፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ገለጸ።

ባለፈው የአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ፣ በአፋር እና ዐማራ ክልሎች፣ ሦስት የረድኤት ሠራተኞች እንደተገደሉ፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ገለጸ።

ከሦስቱ ሠራተኞች፣ ሁለቱ በአፋር አንዱ ደግሞ በዐማራ ክልል እንደተገደሉ የተናሩት የምክር ቤቱ ዋና ዲሬክተር ኄኖክ መለሰ፣ ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ፣ በቁጥር 40 የሚደርሱ የሰብአዊ ድጋፍ ሠራተኞች መገደላቸውን ተናግረዋል፡፡

ግድያ የተፈጸመባቸው ሠራተኞች ይሠሩባቸው የነበሩትን ተቋማት ከመግለጽ የተቆጠቡት አቶ ኄኖክ፣ ለረድኤት ሠራተኞች ጥበቃ እና ከለላ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

እስከ አሁን፣ ሠራተኞቹ ሰሞኑን እንደተገደሉበት የገለጸ የተራድኦ ድርጅት ባይኖርም፣ ባለፈው ቅዳሜ፣ በዐማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ ተደረገ በተባለ “የተኩስ ልውውጥ”፣ ከተገደሉ ሰላማውያን መካከል አንዱ፣ የረድኤት ድርጅት ሠራተኛ እንደኾነ መዘገባችን ይታወሳል። ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG