በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ያልተመቻቸው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳር እና አጠያያቂው የተቃዋሚዎች ይዞታ


ያልተመቻቸው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳር እና አጠያያቂው የተቃዋሚዎች ይዞታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:22:19 0:00

በኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት በፊት ዐዲስ የአመራር ለውጥ ሲደረግ፣ በፖለቲካ ምኅዳሩ ላይ የታየው የለውጥ ርምጃ አሁን ላይ እንደሌለ፣ በተፃራሪው፥ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የሚዋከቡበትና ለእስር የሚዳረጉበት ኹኔታ ተፈጥሯል፤ ሲሉ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር መብርሃቱ ዓለሙ ይናገራሉ፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸው፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሲቪል ማኅበራት ዘርፍ ሓላፊ ሚኒስትር አቶ መለሰ ዓለሙ በበኩላቸው፣ አሁን በአገሪቱ የሰፋ የፖለቲካ ምኅዳር ተፈጥሯል፤ ይላሉ፡፡ ገዥው ፓርቲ፣ ለአንዳንድ ተቃዋሚዎች ሥልጣን በማጋራት፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ለማዳከም ተጠቀሞበታል፤ በሚል የሚቀርበውን ወቀሳ አስተባብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያደርጉትን ተሳትፎ በበላይነት የሚመራው፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች እንዲፈቱና የፖለቲካ ምህዳሩ ለሁሉም እኩል እንዲሆን እየሠራ መኾኑን የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ይገልጻሉ። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳር እና አጠያያቂው የተቃዋሚዎች ይዞታ ዙሪያ

ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG