ከህንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ የሕጻናት የሳል ሽሮፕ 70 ለሚሆኑ ሕጻና የሞት ምክንያት መሆኑን የጋምቢያ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አህማዱ ላሚን እንዳሉት፣ ወደ ሀገር ውስጥ በገባው መንድሃኒት ላይ መደረግ የነበረበት የጥራት ቁጥጥር በተገቢው ሳይደረግ መቅረቱን አስታውቀዋል።
በሹሮፕ ውስጥ በከፍተኛ ደርጀ ኩላሊትን ሊጎዱ የሚችሉ መርዛማ ነገሮች መገኘታቸውን፣ በላቦራቶር በተደረገ ምርመራ መረጋገጡን፣ የዓለምን ጤና ድርጅት አስታውቋል።
ህንድ የራሷን ምርመራ አከናውና ሹሮፑን አምርቷል የተባለውን የመድሃኒት ፋብሪካ መዝጋቷ ታውቋል።
መድረክ / ፎረም