በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስድስት ፍልሰተኞች በጀልባ አደጋ ሕይወታቸው አለፈ


ፎቶ ፋይል (ኤፒ)
ፎቶ ፋይል (ኤፒ)

ወደ ስፔን ለመሻገር ከሞከሩ 54 የሚሆኑ ፍልሰተኞች ውስጥ፣ ይጓዙበት የነበረች ጅልባ ከዓለት ጋር በመጋጨቷ፣ ስድስቱ ሰምጠው ሕይወታቸው እንዳለፈ የሞሮኮ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ከአደጋው የተረፉት 48 የሚሆኑት ፍልሰተኞች ወደ ባህር ዳርቻ ተወስደው የመጀመሪያ የሕክምና ርዳታ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል።

ሟቾቹ ሞሮኳውያን መሆናቸውን የሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች ማሕበር አስታውቋል።

በሌላ ጀልባ ሲጓዙ የነበሩ 40 ፍልሰተኞች ትናንት ቅዳሜ ስፔን መድረሳቸውን ማሕበሩ ጨምሮ አስታውቋል።

በአየር የሚነፉ እና ከፍተኛ ፍጥነት ያላቸው ጀልባዎች ለረጅም ግዜ አደንዛዥ እጾችን ከሞሮኮ ወደ አውሮፓ ለማዛወር እንደሚያገለጉ ሲታወቅ፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ፍልሰተኞችን ለማሻገር በመዋል ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

በዚህ ወር ውስጥ በአንድ ሳምንት ብቻ 900 የሚሆኑ ፍልሰተኞችን መታደጋቸውንና አብዛኞቹም ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት የመጡ መሆናቸውን የሞሮኮ ባህር ኃይል አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG