በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን የሮኬት ጥቃት 20 ተገደሉ


ካርቱም ከአየር ድብደባ በኋላ ፎቶ ፋይል (ሮይተርስ)
ካርቱም ከአየር ድብደባ በኋላ ፎቶ ፋይል (ሮይተርስ)

በሱዳን፤ በዳርፉር እና ሰሜን ኮርዶፋን ተብሎ በሚጠራው ክልል በደረሰ የሮኬት ጥቃት፣ ቢያንስ 20 የሚሆኑ ሰዎች እንደተገደሉ ጠበቆች እና የሕክምና ሠራተኞች ትናንት አስታውቀዋል።

ጥቃቶቹ በዳርፉር ትላልቅ ከተሞች እና በሰሜን ኮርዶፋን ክልል ደግሞ በሆስፒታል አቅራቢያ መድረሱ ታውቋል።

የሱዳን የሐኪሞች ሕብረት እንዳስታወቀው፣ ዓርብ ማለዳ የጀመረው ጥቃት በአራት ሆስፒታሎች አቅራቢያ ሲፈጸም አራት ሰዎች ሲሞቱ፣ 45 ደግሞ ቆስለዋል።

በዳርፉር ዋና መዲና ናያላ ደግሞ፣ በሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ፣ 16 ሰዎች በሮኬት ድብደባ መሞታቸውን የጠበቆች ሕብረት አስታውቋል። ቢያንስ አንድ ሰው ደግሞ በአልሞ ተኳሽ ተመቶ ሕይወቱ እንዳልፈ ማሕበሩ ገልጿል።

ከቻድ ጋር በሚዋሰነው ምዕራብ ዳርፉር፣ ጦርነቱ ከጀመረ አንስቶ አልሞ ተኳሾች ከፎቅ ጣራ ላይ በመሆን ነዋሪዎች ላይ እንደሚተኩሱ ተነግሯል። በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ድንበሩን ተሻግረው ወደ ቻድ ገብተዋል።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በተፈናቀሉባት ሱዳን፣ ረሃብ ከፍተኛ ስጋት መደቀኑን የረድኤት ተቋማት በማስጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG