በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሩስያ-አፍሪካ መሪዎች ጉባዔ የዩክሬኑ ጦርነት ትልቅ ትኩረት እንደሚስብ ተነገረ


 በሶቺ የተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባዒ የደቡብ አፍሪካው መሪ ሲሪል ራማፎሳና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑትን _ ፎቶ ፋይል
በሶቺ የተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባዒ የደቡብ አፍሪካው መሪ ሲሪል ራማፎሳና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑትን _ ፎቶ ፋይል

የአፍሪካ መሪዎች በመጪው ሳምንት ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ጋር ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ላይ ጉባዔ ይቀመጣሉ፡፡

ጉባዔው “የሰላም የደህንነት እና የልማት ትብብራቸውን የሚያጠናክሩበት ይሆናል” ተብሎለታል፡፡

የሩሲያ አፍሪካ ጉባኤው የሚደረገው ሞስኮ በዩክሬን የምታካሂደውን ጦርነት በቀጠለቸበት በዚህ ወቅት ነው፡፡

ጦርነቱ በበርካታ የአፍሪካ አገሮች የምግብ እና ነዳጅ ዋጋ መናር አስከትሏል፡፡

በዚህ ሳምንት ሩሲያ የዩክሬን ዕህል ለዐለም ገበያ እንዲቀርብ ካደረገው ከጥቁር ባህር የእህል ስምምነቱ መውጣቷም የዋጋ ንረቱን ሊያባብሰው እንደሚችል ተመልክቷል፡፡

ተንታኞች ዓለም አቀፍ ጉባዔዎች የፖለቲካ ትያትር መተወኛ መድረኮችም ጭምር መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡

በጆሃንስበርግ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ጥናት ተቋም የአፍሪካ ሩሲያ ፕሮጀክቶች የሚመሩት ስቲቨን ግሩዝድ ለቪኦኤ እንደተናገሩት፣ “የሴንት ፒተርስበርጉ ጉባኤ ስኬት የሚለካው በጉባኤው በሚገኙት የአፍሪካውያን መሪዎች ብዛት ይሆናል፡፡”

የተሳታፊዎቹ መሪዎች ብዛት ትልቅ ትኩረት እንደሚስብም ግሩዝድ አያይዘው ገልጸዋል፡፡

ሶቺ ላይ በተካሄደው የሩስያ እፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ላይ አርባ ሦስት የአፍሪካ ርዕሳነ ብሄራት የተገኙት፣ ሩስያ እ አ አ በ2019 ዓም ዩክሬን ላይ ገና ወረራ ባልከፈተችበትና የተለየ የዐለም ሁኒታ ላይ እያለች ነበር ሲሉ ተንታኙ አስታውሰዋል፡

በዋሽንግተን በሚገኘው የስትራቴጂክ እና አለም አቀፍ ጥናት ማዕከል የአፍሪካ ፕሮግራምን የሚመሩት ኤምቬምባ ዲዞሌል ይህ ትልቅ ውይይት ይሆናል ብለዋል።

ዲዞሌል “እነሱ (ሩሲያውያን) በዩክሬን እየሆነ ባለው ነገር እና በተለይም በአፍሪካውያን ዘንድ ባለው የሸቀጦች ዋጋ - እንዲሁም ቫግነር እና የመሳሰሉት ጉዳዮች በሚያስከትሉት ግጭቶች ከፍተኛ ጫና ውስጥ ወድቀዋል።” ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

የንግድ ልውውጥ ጉዳይም አንዱ መናጋገሪያ ሊሆን እንደሚችልም ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG