በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞው የብአዴን አመራር እና የጥረት ኮርፖሬት ሥራ አስኪያጅ ታደሰ ካሳ ከእስር ተፈቱ


የቀድሞው የብአዴን አመራር እና የጥረት ኮርፖሬት ሥራ አስኪያጅ ታደሰ ካሳ ከእስር ተፈቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:25 0:00

ከጥረት ኮርፖሬት ጋራ ተያይዞ፣ በእስር ላይ የነበሩት አቶ ታደሰ ካሳ(በስፋት በሚታወቁበት አጠራር ታደሰ ጥንቅሹ)፣ ዛሬ ከእስራት እንደተለቀቁ፣ ጠበቃቸው አስታወቁ፡፡

አቶ ታደሰ ካሳ፣ በቀረበባቸው ክሥ ጥፋተኛ ተብለው፣ ላለፉት አራት ዓመት ከስድስት ወር፣ በባሕር ዳር እና በዐዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች በእስር እንደቆዩ ጠበቃቸው ገልጸዋል፡፡

የቀድሞው፣ የብሔር አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ብአዴን) ከፍተኛ አመራር ታደሰ ካሳ፣ ከእስር እንዲፈቱ፣ የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት፣ ውሳኔ ያስተላለፈው፣ ባለፈው ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ነበር፡፡

በውሳኔው መሠረት፣ አቶ ታደሰ ካሳ፣ በዛሬው ዕለት ከእስር ተፈተው ከቤተሰቦቻቸው ጋራ መቀላቀላቸው ታውቋል፡፡

የቀድሞው ጥረት ኮርፖሬት ሥራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ ካሳ፣ ከኮርፖሬቱ ጋራ ተያይዞ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክሥ፣ በዐማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለው፣ ስምንት ዓመት ከአምስት ወር ተፈርዶባቸው እንደነበር፣ ጠበቃቸው ሕይወት ሊላይ ገልጸዋል፡፡

ጠበቃቸው፣ ውሳኔውን በመቃወም በይግባኝ ሲከራከሩ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ የሥር ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ተሽሮ መለቀቃቸውን ተናግረዋል።

በባሕር ዳር ማረሚያ ቤት፣ ለሦስት ዓመታት የቆዩት አቶ ታደሰ፣ በጤና ችግር የተነሣ፣ ከጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም. ጀምሮ፣ ወደ ዐዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተዛውረው ሕክምናቸውን ሲከታተሉ እንደቆዩ፣ ጠበቃ ሕይወት ተናግረዋል፡፡

አቶ ታደሰ፣ ከአራት ዓመት ከስድስት ወር የእስር ቆይታ በኋላ፣ በዛሬው ዕለት፣ ከእስር ተፈተው ከቤተሰቦቻቸው ጋራ መቀላቀላቸውን፣ ጠበቃቸው አያይዘው ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ፣ በተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ ሓላፊነቶች ላይ ከአገለገሉት የቀድሞ ባለሥልጣናት አንዱ አቶ በረከት ስምዖን፣ በጥረት ኮርፖሬት ላይ ፈጠሩት በተባለው የሀብት ብክነት ወንጀል፣ የስድስት ዓመት እስር እና የ10ሺሕ ብር ቅጣት ተላልፎባቸው፣ ከአራት ዓመት እስር በኋላ፣ ባለፈው ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም. በአመክሮ መለቀቃቸው ይታወሳል፡፡

ከፍተኛ ባለስልጣናቱ አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ከጥረት ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢነትና የዋና ሥራ አስፈፃሚነት ኃላፊነታቸው ጋር በተያያዘ ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በቁጥጥር ስር የዋሉት ጥር 2011 ዓ.ም ነበር፡፡

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG