በሶማሊያ፣ እስላማዊው ታጣቂ ቡድን አል-ሻባብ፣ በደቡብ ምዕራባዊዋ ባይዶዋ ከተማ፣ የመግቢያ እና መውጫ መንገዶችን መዝጋቱን፣ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼኽ መሐሙድ አውግዘዋል።
ታጣቂው ቡድን፣ ወደ ባይዶዋ አቅርቦት እንዳይገባና እንዳይወጣ በማድረጉ፣ አስቀድሞም ድርቁ እና የጸጥታው መደፍረስ ያስከተለውን ረኀብ አባብሶታል።
አሕመድ መሐመድ ከሞቃዲሾ ያጠናቀረውን ሪፖርት ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።