በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ


ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:48 0:00

ኢትዮ ቴሌኮም በ2015 ዓ.ም. በጀት ዓመት፣ 75ነጥብ8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።የበጀት ዓመቱን መጠናቀቅ አስመልክቶ፣ ዛሬ ማክሰኞ፣ ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው ኢትዮ ቴሌኮም፣ ገቢው ካለፈው ዓመት ጋራ ሲነጻጸር፣ በ14ነጥብ5 ቢሊዮን ብር መጨመሩን አስታውቋል።

ላለፉት ስድስት ወራት፣ የማኅበራዊ ትስስር ብዙኃን መገናኛ በመዘጋቱ ምክንያት፣ በደንበኞች ላይ ለደረሰው ጉዳት እና መጉላላት፣ የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬ ሕይወት አያሌው፣ በዚኹ መግለጫ አጋጣሚ ይቅርታ ጠይቀዋል።

በሰሜኑና በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች፣ በቴሌኮም መሠረተ ልማቶች ላይ የደረሰውን ጉዳት ሙሉ ለሙሉ ለመጠገን፣ አሁንም እየተሠራ እንደኾነ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG