በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና እና አሜሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ “በጋራ መሥራት አለብን” አሉ


ቻይና እና አሜሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ “በጋራ መሥራት አለብን” አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:49 0:00

የአየር ንብረት ለውጥ የፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ፣ ቻይና እና አሜሪካ በጋራ መሥራታቸው እጅግ አስፈላጊ ነው፤ ሲሉ፣ የአሜሪካ የአየር ንብረት ልዩ ልዑክ ጃን ኬሪ፣ ለቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ቻንግ፣ ቤጂንግ ላይ ተናግረዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ ባለው ችግር፣ ከቻይና ባለሥልጣናት ጋራ ለመምከር፣ ቤጂንግ የሚገኙት የአሜሪካው የአየር ንብረት ልዩ ልዑክ ጃን ኬሪ፣ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዐቅም ያላቸው ሁለቱ ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ አጀንዳ ትኩረት እንዲያገኝ ማድረግ እንደሚችሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል።

“ፕሬዚዳንት ባይደን፣ የአየር ንብረት አጀንዳ ትኩረት ማግኘት ይችላል፤ የሚል ተስፋ አላቸው። ቻይና እና አሜሪካ፣ በዓለም ትልቅ የኢኮኖሚ ዐቅም ያላቸው ሀገራት ናቸው። በአንጻሩም፣ ግሪንሃውስ ጋዝን በከፍተኛ መጠን በመልቀቅም ሁለቱ ቀዳሚ ሀገራት ናቸው። በመኾኑም፣ ሁለቱ ሀገራት በአንድነት፣ አጣዳፊ መፍትሔ በሚያሻው ጉዳይ ላይ፣ በትብብር መሥራት እንደምንችል ለዓለም ካሳየን እጅግ ጠቃሚ ይኾናል፤” ብለዋል ኬሪ።

ጃን ኬሪ፣ ዛሬ ማክሰኞ፣ ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ቻንግ ጋራ ተወያይተዋል። ቀደም ብለውም፣ ከቻይናው ኮሚኒስት ፓርቲ የውጪ ግንኙነት ሓላፊ ዋንግ ዪ ጋራ ተገናኝተዋል።

በቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ውስጥ እንደ ሁለተኛ ሰው የሚታዩት ዋንግ ሊ፣ “በዓለም ሙቀት መጨመር ምክንያት የተፈጠረውን ትልቅ ፈተና ለመጋፈጥ፣ ቻይና እና አሜሪካ ይበልጥ ተቀራርበው መሥራት አለባቸው፤” ሲሉ ለጃን ኬሪ ነግረዋቸዋል።

በታሪፍ፣ በቴክኖሎጂ አቅርቦት፣ በሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ፣ እንዲሁም ቻይና ራስ ገዝ በኾነችው ታይዋን ላይ በምታሰማው ዛቻ ምክንያት፣ በዩናይትድ ስቴትስ እና በቻይና መካከል፣ ከምንጊዜውም በላይ የተቀዛቀዘ ግንኙነት እንዲፈጠር ኾኗል።

ከፍተኛ መጠን ያለውን ካርቦንዳይኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር የሚጨምረውን የድንጋይ ከሰል በማምረት እና በመጠቀም፣ ቻይና በዓለም ቀዳሚ ናት፡፡ ኾኖም፣ በፀሐይ እና በነፋስ አማካይነት ኃይል በማመንጨት ረገድም፣ ቻይና ብዙ እየሠራች ነው።

XS
SM
MD
LG