በሱዳንና በሳህል ቀጣና እየተካሔዱ ካሉት ግጭቶች፣ በልዩ ልዩ አካባቢዎች እስከሚታዩት የድርቅ፣ የጎርፍ እና ሌሎች አስከፊ የአየር ኹኔታ ክሥተቶች ድረስ፣ አፍሪቃ በፈታኝ ወራት ውስጥ እያለፈች ትገኛለች፡፡
ይኹንና፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ሓላፊ አኪንውሚ አዴሺና፣ በቅርቡ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ባደረጉት ቃለ ምልልስ፥ በአህጉሪቱ ተስፋዎች፣ “የበለጸገውን የተፈጥሮ እና ሰብአዊ ሀብቷን እንዴት በተሻለ መንገድ መጠቀም ይቻላል?” በሚሉ ሐሳቦች ዙሪያ ትኩረት አድርገው ተወያይተዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።