ዘንድሮ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠውን የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ፣ ከግማሽ በመቶ በላይ የኾኑቱ ላለማለፋቸው፣ ሓላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም የተባሉ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተወቃሽ እንደሚኾኑ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ ባለሞያዎች ተናግረዋል፡፡
ከወቀሳው በመለስ ለውጤቱ ማነስ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አለመረጋጋት እና ቀደም ሲል የተከሠተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝም አስተዋፅኦ ሊኖራቸው እንደሚችል ባለሞያዎቹ አክለዋል፡፡
የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ልዩ ልዩ ርምጃዎች እየተወሰዱ እንደኾነ የገለጹት፣ በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመምህራን ትምህርት እና የትምህርት አመራር ማዕከል አስተባባሪ ዶ/ር ደጀኔ ንጉሤ፣ ርምጃው፣ በሥራው ዓለም ሲስተዋሉ የነበሩትን ችግሮች ለመቅረፍ አጋዥ ሚና እንደሚኖረው አመልክተዋል፡፡
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚዲያ እና ኮምዩኒኬሽንስ መምህር ዶር. ጌታቸው ጥላሁን ደግሞ፣ አጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል፣ ከዚኽ መሰሉ ርምጃ ባለፈ፣ ሁሉን አቀፍ ጥረት ማድረግን ይጠይቃል፤ ይላሉ፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።