በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ሠራዊት ተወካዮች የድርድር ፍላጉት አሳዩ


የሱዳን መከላከያ ሠራዊት ተወካዮች እንደገና ከተፋላሚው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ጋር ውይይት ለመቀጠል ወደ ጀዳ ሳዑዲ አረቢያ ተመልሰዋል ሲሉ ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አንድ የመንግስት ምንጭ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

በሱዳን የሚካሄደው ጦርነት ሶስተኛ ወሩን አስቆጥሯል።

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የውይይቱን መቀጠል በተመለከተ ያለው ነገር የለም።

በሳዑዲ አረቢያ እና በአሜሪካ አሸማጋይነት በጀዳ ሲካሄድ የነበረው ውይይት፣ ለበርካታ ግዜያት የተኩስ ማቆም ስምምነቶች ከተጣሱ በኋላ፣ ከሳምንታት በፊት ተቋርጦ ነበር።

በኢጋድ አስተናጋጅነት ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ተደርጎ በነበረው ሱዳንን በተመለከተው ውይይት ላይ እንደማይሳተፍ ካስታወቀ ወዲህ፣ የሱዳን መንግስት እንደገና ወደ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች የመግባቱን ፍላጎት በሳዑዲ በሚገኙ ተወካዮቹ በኩል አሳይቷል።

የሱዳን መንግስት በአዲስ አበባው ምክክር ላይ ያልተገኘው፣ የኬንያው መሪ ዊሊያም ሩቶ የውይይቱ ሊቀ መንበር መሆናቸውን በመቃወም ነበር። ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ያደላሉ ስትል ሱዳን ሩቶን ትከሳለች፡፡

በሁለቱ ኃይሎች መካከል የሚደረገው ውጊያ አሁንም እንደቀጠለ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG