በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትዊተር ገቢ በመቀነስ ላይ ነው


ኢላን መስክ እና የትዊተር ሎጎ (ፎቶ ፋይል)
ኢላን መስክ እና የትዊተር ሎጎ (ፎቶ ፋይል)

በማስታወቂያ ገቢ መቀነስ እና በእዳ መከማቸት ሳቢያ፣ ትዊተር ገንዘብ እያጣ መሆኑን ባለቤቱ ኢላን መስክ ትናንት በዛው በትዊተር አስታውቀዋል።

ትዊተር ምንም ነገር ከማድረጉ በፊት ገቢ የሚገኝበትን ዘዴ መቀየስ አለበት ያሉት መስክ፣ የማስታወቂያ ገቢው 50 በመቶ መቀነሱን አስታውቀዋል።

44 ሚሊዮን ዶላር ከፍለው ባለፈው ዓመት ትዊተርን ከተረከቡና በርካታ የኩባንያውን ከፍተኛ ባለሙያዎች ካባረሩ በኋላ ፣ ማስታወቂያ አስነጋሪዎች ሁኔታው ስላሳሰባቸው ግኑኝነታቸውን አቀዝቅዘዋል። በትዊተር ላይ የሚወጡ መልዕክቶችን መቆጣጠርን በተመለከተ የተደረገው ለውጥም ለችግሩ አስተዋጽኦ አድርጓል ተብሏል።

ታግደው የነበሩ እና አንዳንድ አጨቃጫቂና ለግጭት መንስሄ የሚሆኑ መልዕክቶችን የሚያወጡ ተጠቃሚዎች፣ ኢላን መስክ ትዊተርን ከተረከቡ ወዲህ ተመልሰዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG