በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና እና ሩሲያ ወታደራዊ ልምምድ ሊያደርጉ ነው


የቻይና የጦር መርከብ ከኢራን እና ሩሲያ ባህር ኃይሎች ጋር ባለፈው መጋቢት ልምምድ በማድረግ ላይ (ፎቶ Reuters on March 17, 2023.)
የቻይና የጦር መርከብ ከኢራን እና ሩሲያ ባህር ኃይሎች ጋር ባለፈው መጋቢት ልምምድ በማድረግ ላይ (ፎቶ Reuters on March 17, 2023.)

የቻይና ተዋጊ መርከቦች፣ ከሩሲያ የባሕር እና አየር ኃይል ጋር ልምምድ ለማድረግ ‘ጃፓን ባህር’ ተብሎ ወደሚጠራው የውቅያኖስ አካል አቅንተዋል ሲል የቻይናው መከላከያ ሚንስቴር አስታውቋል።

“ስልታዊ የውሃ መተላለፊያዎችን ደህንነት ለመጠበቅ” ያለመ ነው ተብሏል።

ወታደራዊ ምክክር እንዲደረግ አሜሪካ የምታቀርበውን ጥያቄ ቻይና ቸል ማለቷን በቀጠለችበት እና፣ መስኮብ ዩክሬንን ከወረረች ወዲህ የተደረገ ከበድ ያለ ወታደራዊ ልምምድ እንደሆነ ተነግሯል።

ቻይና ለልምምድ ያሰማራቻቸው አምስት የጦር መርከቦች እና አራት ከመርከብ ላይ የሚነሱ ሄሊኮፕተሮች መሆናቸውን የቻይናው መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቆ፣ ቀድሞ በተወሰነ ሥፍራ ላይ ከሩሲያ ኃይሎች ጋር ይገናኛሉ ብሏል።

ከዩክሬን ወረራ ቀደም ብሎ፣ የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቻይናው ሺ ጂንፒንግ፣ የአሜሪካንን ተጽዕኖ ለመቋቋም ሲሉ ገደብ የለሽ ትብብር እንደሚያደርጉ አስታውቀው ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG