በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤሉ ጠ/ሚ የልብ መቆጣጠሪያ ተገጠመላቸው


የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ፤ በቂ ውሃ ካለመውሰድ በሚመጣ መዳከም ምክንያት ትናንት ቅዳሜ ሆስፒታል ገብተው፣ የልብ መቆጣጠሪያ መሣሪያ ከተገጠመላቸው በኋላ ዛሬ ተለቀዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩን ያከመው ‘የሸባ ህክምና ማዕከል’ ባወጣው መግለጫ እንዳለው፣ ልብን ጨምሮ የተደረገላቸው ምርመራ ውጤት ጥሩ እንደነበር፣ ነገር ግን የልብ መቆጣጠሪያ መሣሪያው የተተከለላቸው ሆስፒታሉ ጤናቸውን መከታተል እንዲችል ነው ብሏል።

ናታንያሁ ቅዳሜ ዕለት በለቀቁት የቪዲዮ መልዕክት እስራኤላውያን በቂ ውሃ እንዲጠጡ እና ፀሐይ ላይ የሚቆዩበትን ግዜ እንዲያሳጥሩ መክረዋል።

የ73 ዓመቱ ናታንያሁ ወደ ሆስፒታል ከመወሰዳቸው በፊት የሙቀት መጠኑ 38 ዲግሪ ሴልሲየስ ደርሶበት ከነበረው “ሲ ኦፍ ጋለሊ” ከተሰኘው ሃይቅ አካባቢ ነበሩ ተብሏል።

ለበርካታ ሰዓታት ፀሐይ ላይ በመቆየታቸው የማጥወልወል ስሜት እንደተሰማቸው ታውቋል።

ሳምንታዊ የእስራኤል ካቢኔ ስብሰባም ወደ ነገ ሰኞ ተላልፏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG