በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ መቐለ ለመጓዝ መከልከላቸውን የየገለፁት አባ ሠረቀ ብርሃን የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎትን ከሠሡ


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በልዩ ልዩ መምሪያዎች ላይ በዋና ሓላፊነት ተመድበው ሲሠሩ የቆዩትና በኋላም ኑሯቸውን በአውስትራሊያ አድርገው፣ በዩቲዩብ ብዙኃን መገናኛ አማካይነት በሚሰጧቸው አወዛጋቢ አስተያየቶች የሚታወቁት፣ ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል፣ ከትላንት በስቲያ ማለዳ ዐዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከደረሱ በኋላ መዳረሻዬ ነው ወዳሉት መቐለ እንዳይሔዱ መከልከላቸውን ገለጹ።

የጉዞ ክልከላው የተደረገባቸው፣ በመንግሥት የደኅንነት ሠራተኞች እንደኾነ የገለጹት ጠበቃቸው፣ በብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ላይ ክሥ እንደመሠረቱ ተናግረዋል።

የቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ከጉዟቸው መከልከል፣ የፊታችን እሑድ፣ ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ.ም. የትግራይ ክልል አህጉረ ስብከት አራት ሊቃነ ጳጳሳት በአኵስም ለመፈጸም ቀጠሮ ከያዙለትና ሕገ ወጥ እንደኾነ በቅዱስ ሲኖዶስ ከተገለጸው የዐሥር ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ጋራ መያያዙ፣ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡

ሙሉ ዘገባን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG