በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል የጦርነቱ ክትያ የኾነው የረኀብ አደጋ ተባብሶ ቀጥሏል


በትግራይ ክልል የጦርነቱ ክትያ የኾነው የረኀብ አደጋ ተባብሶ ቀጥሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:58 0:00

አንዲት እጅግ የከሳች ሕፃን፣ ጥቅልል ብላ ከተኛችበት የሆስፒታል አልጋ ላይ ሳለች ለመተንፈስ ስትታገል ትታያለች። ወላጅ አባቷ፥ የልጅነት ለስላሳ ፊቷን ሲደባብስ፣ እናቷ በበኩሏ በተቀመጠችበት ታለቅሳለች።

ከፊት ለፊት ‘ቆንጆ’ የሚል ጽሑፍ የሚነበብበት ሮዝ ቀለም ያለው ሹራብ የለበሰችው አዳጊ ጽጌ ሲሳይ፥ 10 ዓመት ቢሞላትም ክብደቷ የሚመዝነው ግን 10 ኪሎ ግራም ብቻ ነው።

መነሻውን በክልሉ አድርጎ ለሁለት ዓመታት በተካሔደው ጦርነት እና በተከተለው ድርቅ ክፉኛ በተጎዳው ክልል፣ ለተከሠተው ከፍተኛ የምግብ እጥረት፣ ዐዲስ ሰለባ የኾነችው ሕፃን ለኅልፈት መዳረጓን ሐኪሟ ይናገራል።

የሮይተርስ የዜና ወኪል ወደ ሥፍራው የላካቸው ዘጋቢዎች፣ መቐለን ጨምሮ ተፈናቃዮች ያሉባቸውን የተለያዩ ከተሞች እና አካባቢዎች ተዘዋውረው ከተመለከቱ በኋላ ያጠናቀሩት ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል።

XS
SM
MD
LG