በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፓትርያርኩ የተመራ የሰላም ልኡክ በመቐለ ጉብኝት በማድረግ የ20 ሚሊየን ብር ሰብአዊ ርዳታ ለገሰ


በፓትርያርኩ የተመራ የሰላም ልኡክ በመቐለ ጉብኝት በማድረግ የ20 ሚሊየን ብር ሰብአዊ ርዳታ ለገሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:41 0:00

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አባ ማትያስ የሚመሩት የቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ልዑክ፣ ዛሬ ጠዋት መቐለ ገብቷል፡፡በቅዱስነታቸው ለተመራው የሰላም ልኡክ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አቀባበል ቢያደርግም፣ የትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት እና የሥራ ሓላፊዎች ግን በሥነ ሥርዐቱ ላይ አልተገኙም፤ ከፕሬዚዳንቱ አቶ ጌታቸው ረዳ ጋራ በፕላኔት ሆቴል በተደረገው አጭር ውይይትም ላይ አልተሳተፉም፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አባ ማትያስ የሚመሩት የቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ልዑክ፣ ዛሬ ጠዋት መቐለ ገብቷል፡፡

በቅዱስነታቸው ለተመራው የሰላም ልኡክ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አቀባበል ቢያደርግም፣ የትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት እና የሥራ ሓላፊዎች ግን በሥነ ሥርዐቱ ላይ አልተገኙም፤ ከፕሬዚዳንቱ አቶ ጌታቸው ረዳ ጋራ በፕላኔት ሆቴል በተደረገው አጭር ውይይትም ላይ አልተሳተፉም፡፡

የትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ባለመገኘታቸው ማዘናቸውን ያልሸሸጉት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ “ልዩነት በውይይት ነው የሚፈታው፤ ብፁዓን አባቶች ቢገኙ መልካም ነበር፤” ብለዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳም፣ ልዩነት በውይይት መፈታት ኣለበት ብለው እንደሚያምኑና የትግራይ ክልል አባቶች ወደ ውይይት እንዲመጡ ጥረት እንደሚያደርጉ፣ ኾኖም ሊያስገድዷቸው እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ለክልሉ ተጎጂዎች እንዲውል የለገሰውን የ20 ሚልዮን ብር ሰብአዊ ርዳታ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አባ ማትያስ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት አስረክበዋል፤ ልኡካኑ ተፈናቃዮችም ጎብኝተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG