በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን የከተማ ውስጥ የአየር ጥቃት ቢያንስ 22 ሰዎች ተገደሉ


በሱዳን በሁለቱ ተፋላሚ ጀኔራሎች መካከል የሚካሄደው ጦርነት ቀጥሏል
በሱዳን በሁለቱ ተፋላሚ ጀኔራሎች መካከል የሚካሄደው ጦርነት ቀጥሏል

በሱዳን ትናንት ቅዳሜ ከተማ ውስጥ በተፈጸመ የአየር ጥቃት ቢያንስ 22 ሰዎች መገደላቸውንና ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መቁሰላቸውን የጤና ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡

ጥቃቱ የተፈጸመው የካርቱም አጎራባች በሆነችው ኦምዱርማን፣ ዳር አስ ሰላም ከተማ መሆኑን የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አመልክቷል ፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አደጋውን አስመልክቶ ባወጣው ተንቀሳቃሽ የቪዲዮ ምስል፣ መሬት ላይ የተደረደሩ በአንሶላ የተሸፈኑ የሰዎችን አስክሬን አሳይቷል፡፡

ከፍርስራሾች ውስጥ የሞቱ ሰዎችን አካላት ጎትተው ለማውጣት የሚታገሉ እንዲሁም የቆሰሉትን የሚረዱ እና የሚያለቅሱም ሰዎች በተቀንሳቃሹ ምስል እንደሚታዩ ተመልክቷል፡፡

በሁለቱ የሥልጣን ተቃናቃኝ የሱዳን ጀኔራሎች መካከል የሚደረገው ውጊያ በተጀመረ ሶስት ወራት ውስጥ የትናንቱ እጅግ አስከፊ ከሆኑ የአየር ጥቃቶች አንዱ ነው ተብሏል፡፡

ባላፈው ወርም ካርቱም ውስጥ በደረሰው ተመሳሳይ የአየር ጥቃት ቢያንስ 17 ሰዎች ሲገደሉ ከእነዚህ አምስቱ ህጻናት መሆናቸው ተዘግቧል፡፡

የፈጥኖ ደራሹ ጦር ለቅዳሜውና ሌሎች ጥቃቶች ተጠያቂው በተቀናቃኝነት የሚፋለመው ሠራዊት መሆኑን አስታውቋል፡፡

በአካባቢው ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የገለጹ ነዋሪዎች፣ ሠራዊቱ ለፈጥኖ ደራሹ ወሳኝ የሆነውን የአቅርቦት መስመር ለመቁረጥ እየሞከረ ነው ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ ጥቃቱን ያወገዙ መሆኑን ረዳት ቃል አቀባያቸው ፋርሃን ኻቅ ትናንት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG