በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማላዊ ፕሬዘዳንት ሀገራቸው ስዋሂሊ ቋንቋ ትምህርት እንድትጀምር አዘዙ


የማላዊ ፕሬዘዳንት ላዛረስ ቻክዌራ ሰኔ 2015 ዓ.ም
የማላዊ ፕሬዘዳንት ላዛረስ ቻክዌራ ሰኔ 2015 ዓ.ም

የማላዊ ፕሬዘዳንት ላዛረስ ቻክዌራ የሀገሪቱ የትምህርት ባለስልጣናት በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ የስዋሂሊ ቋንቋን እንዲያካትቱ አዘዙ። ፕሬዘዳንቱ ይኸንን ያሉት ሀገሪቱ ስዋሂሊ ቋንቋን ከሚናገሩ ሀገራት ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት ለማሳለጥ ነው።

ፕሬዘዳንቱ “አስተዳደሬ ስዋሂሊ ቋንቋን ከእህት ሀገር ታንዛኒያ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ሲል በማላዊ ሊያስተዋውቅ ነው፤ በማለት ለክብርት የታንዛኒያ ፕሬዘዳንት ማሳወቁን ስነግራቹ በደስታ ነው” ብለዋል። “የትምህርት ሚኒስተሬ አተገባበሩን እና ፖሊሲውን እንዲያዘጋጅ ታዟል” ሲሉም አክለዋል።

የማላዊ የትምህርት ባለሞያዎች ስዋሂሊን ቋንቋን መማር በብዙ የአፍሪካ ሀገራቶች የሚነገር ቋንቋ በመሆኑ ማላዊ የንግድ ትስስሯን እንድታሳድግ ያግዛል ብለዋል።

የታንዛኒያ ፕሬዘዳንት ሳሚያ ሀሰን ሀሙስ ዕለት በሊሎንግዌ የማላዊ 59ኛ ዓመት የነጻነት ቀን ሲከበር የክበር እንግዳ ሆነው ተገኝተዋል። ፕሬዘዳንት ሳሚያ በማላዊ የሶስት ቀናት ጉብኝት አድርገዋል። ፕሬዘዳንቷ ታንዛኒያ ማላዊ የስዋሂሊ ቋንቋን ማስተማር ለመጀመር በሚያስፈልጋት ሁሉ እናግዛለን ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG