በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ክልል ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር ያላገኙ አርሶ አደሮች አቤቱታ


በኦሮሚያ ክልል ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር ያላገኙ አርሶ አደሮች አቤቱታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:01 0:00

በምዕራብ፣ በሰሜን፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፣ በምሥራቅ ወለጋ እና ቡኖ በደሌ ዞኖች የሚገኙ አንዳንድ አርሶ አደሮች፣ የገጠማቸው የማዳበሪያ እጥረት ካልተቀረፈ፣ “ረኅብ ሊያጋጥመን ይችላል” የሚል ስጋት አላቸው። የዘር ወቅት ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ መቅረቱ ስጋታቸውን እንዳባባሰባቸው ተናግረዋል።

በምዕራብ ሸዋ ዞን የግብርና ጽሕፈት ቤት እና የኅብረት ሥራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ ጽሕፈት ቤት፣ በአገር አቀፍ ደረጃ የማዳበሪያ አቅርቦቱ አነስተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

ከአርሶ አደሩ ለተነሡት ቅሬታዎች፣ ከኦሮሚያ ግብርና ቢሮ፣ ከኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ እና ከግብርና ሚኒስቴር፣ በተደጋጋሚ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት፣ ለዛሬ አልተሳካም።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ፣ የአርሶ አደሮቹ ቅሬታ እንደደረሰው ገልጾ፣ መንግሥት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጥ ጠይቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG