በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትንሿ ግን ፈታኟ የኢትዮጵያውያን የድንኳን ቤተ መዘክር በዳላስ


ትንሿ ግን ፈታኟ የኢትዮጵያውያን የድንኳን ቤተ መዘክር በዳላስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:58 0:00

ከዋይሊ ስታዲየም ጀርባ በተቀለሰችው አነስተኛ ድንኳን ውስጥ፥ የኢትዮጵያን ታሪክ፣ የሕዝቦችን ባህል እና ትውፊት የሚያስተዋውቁ መዛግብት፣ ምስሎች እና ቁሳቁሶች ተገጥግጠዋል። የአነስተኛዋ ቤተ መዘክር አስጎብኚ ዲያቆን ፍሬው ሰይፉ፣ ከመስሕቦቹ ጀርባ ያለውን ታሪክ ለጎብኚዎች በትጋት ያስረዳል።

ትንሿ ድንኳን፥ ዳላስ፣ ቴክሳስ ላይ የተቋቋመው፥ “ዐድዋ የባህል እና የታሪክ ኅብረት” ተቋም መስሕቦች፣ ናሙና ናት። የተቋሙ መሥራች ዲያቆን ፍሬው ሰይፉ፣ የዛሬ ስምንት ዓመት ገደማ፣ ከትውልድ ሀገሩ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ሲመጣ ከሸከፋቸው ሕልሞቹ መካከል አንዱ፣ ተቋሙን እውን ማድረግ እንደኾነ ይናገራል።

በውስጡ የያዛቸውን ታሪክ እና ባህል አንጸባራቂ ቁሳቁሶችን ከማሰባሰብ ጀምሮ፣ በስደት ተለዋዋጭ የሕይወት ኹኔታ ውስጥ የሚፈጠሩ ተግዳሮቶችን አልፎ መሰል ሥራን ማስቀጠል፣ ቀላል ልፋትን አይጠይቅም። ዲያቆን ፍሬው፣ አሜሪካ ተወልደው የሚያድጉ ልጆችን የማንነት ጥያቄ ለመመለስ በእጅጉ መሻቱ፣ በፈታኙ ሥራ እንዲገፋበት ጉልበት እንደኾነው ይናገራል።

ዲያቆን ፍሬው፣ ታሪክንና ባህልን ዘካሪ ተቋም ከመትከል ባለፈ፣ በዕለታዊ ሕይወቱም፣ የሀገር ባህል አምባሳደርነቱን ዘንግቶ የሚያውቅ አይመስልም። ዓመቱን ሙሉ፣ የኢትዮጵያን ሕዝቦች ባህል በሚያንጸባርቁ አልባሳት ደምቆ መታየቱ ለዚያ ነው። ከ130 በላይ ባህላዊ አልባሳት እና መጫሚያዎች በእጁ እንደሚገኙ ይናገራል።

ወደ ዳላስ፣ ቴክሳስ ከሰሞኑ ያቀናው ሀብታሙ ሥዩም፣ ከዲያቆን ፍሬው ጋራ ያደረገው ቆይታ ከሥር ተያይዟል።

XS
SM
MD
LG