በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፈረንሳይ ውስጥ በፖሊስ ጥይት የተገደለው ታዳጊ ወጣት ቀብር ተፈጸመ


የወጣቱን መገደል ተከትሎ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ለጥበቃ የተሰማሩ ፖሊሶች/ ሰኔ 25/2015 ዓ.ም
የወጣቱን መገደል ተከትሎ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ለጥበቃ የተሰማሩ ፖሊሶች/ ሰኔ 25/2015 ዓ.ም

ፈረንሳይ ናንቴር ከተማ ውስጥ ባለፈው ማክሰኞ በፖሊስ ተተኩሶበት የተገደለው ታዳጊ ወጣት ቀብር ትናንት ቅዳሜ ተፈጽሟል።

አልጄሪያዊ ወይም ሞሮኳዊ እንደሆነ በተነገረው የአስራ ሰባት ዓመቱ ናሂል መገደል፣ ፈረንሳይ ስርዐታዊ ዘረኝነት የሰፈነባት አገር አድርገው በሚመለከቷት ዘንድ ተቃውሞ አስነስቷል።

የናሂል እናት ለ“ፍራንስ 5” ቴሌቭዥን ጣቢያ እንደተናገሩት፣ "ፖሊሱ አረብ የሚመስል ልጅ ሲያይ ሊገድለው ፈለገ ፥ የሆነው ያ ነው" ብለዋል። ፖሊሱ የሟቹን ቤተሰብ ይቅርታ መጠየቁ ተዘግቧል።

ትናንት ቅዳሜ ማታ የተቃውሞ ሰልፉ ጋብ ማለቱ ተገልጿል። ዓርብ ማታ የታሰሩት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ቁጥር ከ1300 በላይ የነበረ ሲሆን ትናንት ማታ የታሰሩት 700 መሆናቸው ተመልክቷል።

የፈረንሳይ መንግሥት ባለስልሥጣናት እንዳስታወቁት በሁለቱ ቀናት በሀገሪቱ ዙሪያ 45 ሺህ ፖሊሶች ለጥበቃ ተሰማርተዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ቢሮ ፣ “ፈረንሳይ ውስጥ የተቀሰቀሰው አለመረጋጋት በሀገሪቱ የህግ አስከባሪ ዘርፍ ውስጥ ላለው ስር የሰደደ ዘረኝነት መፍትሄ እንድትፈልግ ዕድል ይሰጣታል" ማለቱ ተጠቅሷል።

የአገሪቱ ፕሬዚደንት ኢማኑዌል ማክሮን በሀገራቸው "ስርዐታዊ ዘረኝነት አለ " የሚለውን ውንጀላ አጥብቀው ያስተባብላሉ።

XS
SM
MD
LG