በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባልቲሞር ውስጥ 30 ሰዎች በጥይት ተመቱ


ባልቲሞር ውስጥ ድርጊቱ የተፈፀመበትን ቦታ የሚያሳይ ምስል/ሰኔ 25/2015 ዓ.,ም
ባልቲሞር ውስጥ ድርጊቱ የተፈፀመበትን ቦታ የሚያሳይ ምስል/ሰኔ 25/2015 ዓ.,ም

በዩናይትድ ስቴትስ ሜሪላንድ ግዛት፣ ባልቲሞር ውስጥ ብሩክሊን ሆምስ በተባለ መንደር በተዘጋጀ የሰፈር ድግስ ላይ፤ ዛሬ ሌሊት 30 ሰዎች በጥይት መመታታቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ሁለቱ ወዲያው ሲሞቱ፣ ሦስቱ በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ፖሊስ ገልጿል።

ከተጎጂዎች መካከል 20ዎቹ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን፣ የባልቲሞር ፖሊስ ተጠባባቂ ኮሚሽነር ሪቻርድ ተናግረዋል።

የድርጊቱን ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር እስኪውሉ ፍለጋቸውን እንደማያቆሙ ለሲኤንኤን የቴሌቭዥን ጣቢያ የገለፁት የከተማዋ ከንቲባ ብራንደን ስኮት፤ የጦር መሳሪያ ቁጥጥርን አስፈላጊነት በተመለከተ በባልቲሞር ብቻ ሳይሆን በመላ አገሪቱ ሊታሰብበት እንደሚገባ አሳስበዋል።

XS
SM
MD
LG