በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል የመጀመሪያው ዙር የወታደሮች ቅነሳን አጠናቀቀ


ፎቶ ፋይል (ATMIS)
ፎቶ ፋይል (ATMIS)

በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል የመጀመሪያው ዙር የወታደሮች ቅነሳን ማጠናቀቁን አስታወቀ።

አትሚስ በመባል የሚታወቀው በሶማሊያ የአፍሪካ የሽግግር ልዑክ ትናንት እንዳስታወቀው፣ ሰባት ወታደራዊ ሰፈሮችን ለቆ ለሶማሊያ የጸጥታ ኃይሎች አስረክቧል። ወደፊት አጠቃላይ የጸጥታ ሥራውን ለሶማሊያ ጦር የማስረከቡ እና ሙሉ ለሙሉ የመውጣቱ ጅማሬ እንደሆነ ተጠቁሟል። ትናንት በተጠናቀቀው የፈረንጆች ሰኔ ወር፣ 2000 ወታደሮችን የማሰወጣቱ አንደኝው ዙር ቅነሳ ተጠናቋል ሲል ልዑኩ ያወጣውን መግልጫ ጠቅሶ ኤኤፍፒ ዘግቧል።

የመጀመሪአው ዙር ወታደራዊ ሠፈሮቹን የማሥረከቡ ሥራ ከሶማሊያ የሽግግር ዕቅድ እና የተባበሩት መንግስታት ካወጣው የውሳኔ ሃሳብ አንጻር እጅግ አስፈላጊ እርምጃ እንደነበር የልዑኩ የአቅርቦት ሃላፊ ቦስኮ ሲቦንዳቪ ተናግረዋል።

የጸጥታው ም/ቤት ባለፈው ማክሰኞ የአፍሪካ ኅብረትን ኃይል ቆይታ ለተጨማሪ 6 ወር አስረዝሟል። በመጪው መስከረም መጨረሻ ግን 3 ሺሕ ወታደሮችን ከሶማሊያ እንዲያስወጣ ይጠበቅበታል።

ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ እንዲሁም ከሌሎች የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ 19 ሺሕ ወታደሮች በሰላም አስከባሪ ልዑክ ውስጥ ሲኖሩ፣ እስከ ሚቀጥለው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ድረስ ሙሉ ለሙሉ ለቀው ይወጣሉ ተብሏል።

XS
SM
MD
LG