በኬንያ ትናንት ዓርብ ምሽት በደረሰ የመኪና አደጋ 52 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል ተብሏል።
በምዕራብ ኬንያ አንድ ትልቅ ዕቃ ጫኝ መኪና ሌሎች መኪኖችን በመደዳ በመግጨቱ አደጋው እንደተከሰተ ታውቋል።
የቤት መኪኖች፣ ሚኒባሶች፣ ሞተር ብስክሌቶች እና ሌሎችም ዕቃ ጫኝ መኪኖች እርስ በእርስ በመጋጨታቸው 52 ሰዎች ሕይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።
በአካባቢው በጣለው ኃይለኛ ዝናብ ምክንያት የአደጋ ሥራው መጓተቱን ቀይ መስቀል አስታውቋል።
አገሪቱ ከሟች ቤተሰቦች ጋር በመሆን በአሰቃቂ አደጋው ሕይወታቸውን ላጡት ዜጎች በጋራ ታዝናለች ሲሉ ፕሬዝዝደንት ዊሊያም ሩቶ በትዊተር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በህንድ ደግሞ ዛሬ ማለዳ በደረሰ የመኪና አደጋ ቢያንስ 25 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ሰዎችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ አውቶብስ ከተጋጨ በኋላ፣ በእሳት በመቀጣጠሉ ሕይወት ሊጠፋ ችሏል።