በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግዳጅ ወደ አሰብ ስለተመለሱት ኤርትራዊያን


በግዳጅ ወደ አሰብ ስለተመለሱት ኤርትራዊያን
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:02 0:00

በግዳጅ ወደ አሰብ ስለተመለሱት ኤርትራዊያን

ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሁለት መቶ የሚሆኑ ኤርትራዊያን በግዳጅ ወደ ኤርትራ እንዲመለሱ መደረጋቸው እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ።

አድራጎቱ “በስደተኞችና ከለላ ጠያቂዎች ደኅንነት ላይ ሥጋት የደቀነ” እንደሆነም ኮሚሽኑ አመልክቷል።

አዲስ አበባ ውስጥ የሚኖሩ ኤርትራዊያን ስደተኞች በበኩላቸው ሰዎቹን ወደ ኤርትራ የመመለሱ አድራጎት “በእኛም ላይ ይቀጥላል የሚል ስጋት አሳድሮብናል” ብለዋል።

የኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ግን “እንዲመለሱ የተደረጉት ሰዎች ስደተኞችም ከለላ ጠያቂዎችም አይደሉም” ብሏል።

በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘውን ሁኔታ በቅርቡ ጎብኝተው የገመገሙት በኤርትራ የሰብዓዊ መብቶች እና ፍልሰተኞች ተሟጓች ሜሮን እስጢፋኖስ ወደ ያለፍቃዳቸው ወደ አሰብ የተወሰዱት አዲስ አበባ እና አፋር ክልል ውስጥ ታስረው የነበሩ 432 ኤርትራዊያን መሆናቸውን ለቪኦኤ ተናግረዋል።ወደ አሰብ ተባርረዋል

ብዙ ኤርትራዊያን ተይዘው ወደ እሥር ማዕከላት መወሰዳቸውን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንደሚናገሩ የጠቆሙት ሜሮን “በተለያዩ ሰበቦች ከታሰሩት ብዙዎቹ ለማደስም የማይቻሉት ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድና የስደተኛነት ምዝገባ ሰነድ የሌላቸው ናቸው” ብለዋል።

አንዳንዶቹ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እንደሚለቀቁ፣ ሌሎች ደግሞ ስለእነሱ የሚናገር ድርጅት በሌለበት ሁኔታ ከፍተኛ ገንዘብ መክፈል እንደሚገደዱ አመልክተዋል።

ሜሮን እና ወደ አሰብ የተወሰዱ ፍልስተኞችን ያነጋገሩ ሌላ እማኝ ስደተኞቹ አሰብ መወሰዳቸውን አረጋግጠዋል።

ኤርትራውያኑ የፖለቲካ ከለላ እንዳያገኙ የከለከለው መጥፎው የፖሊሲ ክፍል እኤአ በ2019 በሁለቱ ወገኖች መካከል የተካሄደው ስምምነት መሆኑን ሜሮን አክለው ጠቁመዋል።

በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት የሞከሩ ብዙ ኤርትራዊያን ወደ አገር ለመግባት ተከልክለው በድንበሩ መግቢያ ላይ መቅረታቸውና ይህ ደግሞ ኤርትራዊያንን ወደ ኢትዮጵያ በስውር የሚያስገቡ ህገ ወጥ አስተላላፊዎች እንዲፈጠሩ ማድረጉ ተዘግቧል።

ዘገባው የገብረሚካዔል ገብረመድኅን እና የአብርሃም ዘርኧ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG