በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የራያ ወሎ የዐማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለፌዴሬሽን ም/ቤት ያቀረበው የማንነትና የበጀት ጥያቄ


የራያ ወሎ የዐማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለፌዴሬሽን ም/ቤት ያቀረበው የማንነትና የበጀት ጥያቄ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:52 0:00

የራያ አላማጣ እና አካባቢው ዓመታዊ በጀትም ሆነ ድጎማ፣ በትግራይ ክልል በኩል እንዳይሆን፣ የ145ሺሕ ነዋሪዎች ፊርማ አሰባስቦ ለፌዴሬሽን ም/ቤት ማቅረቡን፣ የራያ ወሎ ዐማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ገለጸ፡፡

የኮሚቴው የአደረጃጀት ዘርፍ ሓላፊ፣ የተሰበሰበው ፊርማ፥ የማንንት ጥያቄያችን ይመለስ፤ በጀቱ እና ድጎማው በትግራይ ክልል በኩል ሳይሆን፣ በቀጥታ ይግባልን፤ የሚል እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ ጥያቄው፥ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱን ያልተከተለ ነው፤ ሲል ተችቷል፡፡የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ቢሮ ሓላፊ ረዳኢ ኃለፎም፣ ጥያቄው ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት ከመድረሱ በፊት፣ ለትግራይ ክልል መቅረብ ነበረበት፤ ይላሉ፡፡

ራሱን፣ “የራያ ወሎ የዐማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ” የሚለው አካል ግን፣ ጥያቄውን በ2011 ዓ.ም. ለትግራይ ክልል ቢያቀርብም ምላሽ አለማግኘቱን በማንሣት ይከራከራል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG