በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤጂንግ ቻይናውያንን ወደ ሃገራቸው አስገድዶ የማስመለስ ዘመቻ የተወነጀሉ ተፈረደባቸው


 ፍቶ ፋይል - በግንቦት ወር መጨረሻ ከተከሳሹ አንዱ ዙ ዮንግ፣ ልክ፣ብሩክሊን ውስጥ ከሚገኘው የፌዴራል ፍርድ ቤት ሲወጣ ከፎቶግራፍ አንሺዎች እራሱን ለመከላከል ሲሞክር
ፍቶ ፋይል - በግንቦት ወር መጨረሻ ከተከሳሹ አንዱ ዙ ዮንግ፣ ልክ፣ብሩክሊን ውስጥ ከሚገኘው የፌዴራል ፍርድ ቤት ሲወጣ ከፎቶግራፍ አንሺዎች እራሱን ለመከላከል ሲሞክር

ቤጂንግ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚኖሩ ቻይናውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ለማስገደድ ዘመቻ ይዛለች’ በሚል ‘ዩናይትድ ስቴትስ የምታቀርብባትን ውንጀላ ያሳየ ነው’ ከተባለ ድርጊት ጋራ በተያያዘ ሦስት ሰዎች ጥፋተኛ ሆነው ተገኙ።

የብሩክሊን የፌደራል ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት ያስቻለው ከኅብረተሰብ የተውጣጣ የሕዝብ የዳኝነት ቡድን ነው ብይኑን የሰጠው። ተከሳሾቹ ኒው ጀርሲ ውስጥ በሚኖሩ አንድ የቀድሞ የቻይና ባለሥልጣን የነበሩ ግለሰብ ላይ ተከታታይ ወከባ እና ማስፈራሪያ ዘዴዎችን ተጠቅመዋል’ በሚል ነው የተወነጀሉት።

የክስ ሂደቱ የዩናይትድ ስቴትስ ዐቃብያነ ሕጎችን ጥብቅ ፍተሻ ያደረጉበት የመጀመሪያው ውጤት ነው። ቤጂንግ ‘ከአገር አምልጠው የተሸሸጉ ሰዎችን ለመያዝ የታለመ ነው’ የምትለው ይህ ዘመቻዋ አሥር አመታት የሚጠጋ ጊዜ ያስቆጠረ መሆኑም ተዘግቧል። በማስፈራራት ሰዎች ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ሞክራለች የሚለውን ውንጀላ ግን ቻይና ታስተባብለች።

XS
SM
MD
LG