በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ተስፋ ከቤት ወዲያ” በ“ዓለም አቀፉ የስደተኞች ቀን” 


“ተስፋ ከቤት ወዲያ” በ“ዓለም አቀፉ የስደተኞች ቀን”
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:50 0:00

“ተስፋ ከቤት ወዲያ” በ“ዓለም አቀፉ የስደተኞች ቀን”

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ቀን፣ በዛሬው ዕለት በመላው ዓለም፣ “ተስፋ ከቤት ወዲያ” በሚል መሪ ቃል በመታሰብ ላይ ይገኛል። የመንግሥታቱ ድርጅት፣ በአሁን ሰዓት በዓለም ዙሪያ፣ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሰዎች፣ ከመኖሪያ ቀዬአቸው በተለያዩ ምክንያቶች ተፈናቅለው እንደሚገኙ በቅርቡ አስታውቋል። ስደተኞች እና ቤተ ሰዎቻቸው ምቹ ወደኾኑ መኖሪያዎች እስኪዘዋወሩ ድረስ፣ እጅግ ብዙ ችግሮችን ይጋፈጣሉ።

ጁሊያ ዴንግ፣ ከሰባት ዓመታት በፊት በደቡብ ሱዳን የነበረውን የእርስ በርስ ጦርነት በመሸሽ፣ ከሦስት ልጆቿ ጋራ ወደ ኢትዮጵያ ተሰድዳለች። ይህቺ እናት፣ አሶሳ በሚገኘው ጾሬ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድጋፍ፣ ከሦስት ልጆቿ እና ከእህቷ ጋራ ለአምስት ዓመታት ኖራለች።

በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2021፣ በመልሶ ሠፈራ መርሐ ግብር፣ ልጆቿን ይዛ ወደ ኖርዌይ የመጣችው ጁሊያ፣ “በዚያ ሳለሁ የሚሰጠን የምግብ ራሽን በቂ አልነበረም።” ስትል በጾሬ የነበረው ሕይወቷ ከባድ እንደነበር ታስታውሳለች።

አክላም “ራሽን በሚታደልበት ወቅት፣ ከሰዎች ላይ በርካሽ እገዛና የሌሎቹ ራሽን ማለቅ ሲጀምር፣ ቆጥቤ ያስቀመጥኹትን መልሼ ሸጬ፣ ለልጆቼ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች አሟላ ነበር። ከዚያ በተጨማሪ፣ ለአምስት ዓመታት ያህል በበጎ ፈቃድ ሰዎችን የማገዝ ሥራ ስሠራ፣ 1ሺሕ700 ብር ይከፍሉኝ ነበር። ነገር ግን መደበኛ ክፍያ ስላልኾነ፣ በቂ ብር አይደለም።” ብላለች። ።

ከልጆቿ ጋራ በካምፑ በነበራት ቆይታ፣ የተለያዩ ግጭቶች ነበሩ፤ የምትለው ጁሊያ፣ “በደቡብ ሱዳን ከልጆቼ ጋራ እያለኹ፣ ሰላም አልነበረም። የጎሣ ለጎሣ ብዙ ግጭቶች ነበሩብን።” የምትለው ጁሊያ ኢትዮጵያ ሲደርሱ ትንሽ ሰላም ማግኘታቸውን ትናገራለች። “ቢያንስ ልጆቼ፣ የመሣሪያ ድምፅ አይሰሙም። በካምፑ ውስጥ በስደተኞች መካከል ግን የእርስ በርስ ግጭቶች አሉ። የዲንቃ እና የማባን፣ እንዲሁም የሌሎች ጎሣዎች፣ በኢትዮጵያ ካምፖች ውስጥ ነበሩ። ዘወትር የሚከሠት ነገር ባይሆንም፣ እነርሱ ይጋጩ ነበር። ወደ ሌላ ሀገር የመሔድ ዕድሉን ሳገኝ፣ እንድወስን ያደረገኝ ነገር ይህ የካምፑ ሁኔታ ነው።”

የ34 ዓመቷ ጁሊያ፣ በኖርዌይ፥ ልጆቿ በሰላም ወደ ትምህርት ቤት እንደሚሔዱ፤ እርሷም፥ የምግብ እና የመጠለያ ድጋፍ እየተደረገላት ትምህርቷን መማር መቻሏን በመግለጽ፣ ይህን መሰል ዕድል በማግኘቷ ታመሰግናለች።

በዓለም አቀፉ የስደተኞች ቀን፣ “መንግሥታት፣ ለስደተኞች ተጨማሪ ድጋፍ ለማስገኘት የሚያግዝ መርሐ ግብር ማዘጋጀት ይችላሉ፤ በተለይ ደግሞ ለሕፃናት፡፡ በካምፑ ውስጥ ያሉ ሰዎች፣ እርስ በርሳቸው አይዋደዱም። እነዚህ ሰዎች፣ በኅብረት እንዲኖሩ የሚያቻችል ፕሮግራም ያስፈልጋል። በኅብረት መኖር እና እንዴት መዋደድ እንዳለባቸው ማስተማር አለባቸው።” ስትል የመንግሥታቱ ድርጅት እና ሀገራት ማድረግ አለባቸው የምትላቸውን ነገሮችም አጋርታለች።

አያይዛም፤ “በካምፖቹ ውስጥ ኑሮ እየተወደደ ነው። የሚለበስ ነገር ቢሰጧቸውና በአልባሳት ቢደግፏቸው፣ በተጨማሪም ቤታቸውን ቢሠሩላቸው መልካም ነው። በተለይ ደግሞ፣ ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች እና ወላጆቻቸውን በሞት ላጡ ሕፃናት፣ እነዚያን ድጋፎች ቢያደርጉላቸው፤ እነርሱም ድጋፍ ይሻሉ። አንዳንዶቹ ቤት የላቸውም። በአሶሳ ቤት ለመሥራት የሚያገለግል ሣር ለማጨድም ኾነ ዛፍ ለመቁረጥ፣ ለስደተኞቹ የሚፈቀድ አይመስለኝም። ስለዚኽ፣ አነስ ያሉ መጠለያ ቤቶችን፥ ቤት ለሌላቸው፣ ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች እና ያለወላጅ እና ሞግዚት ብቻቸውን ለሚገኙ ሕፃናት እየቀለሱ ቢያግዟቸው መልካም ነው፡፡” ብላናለች።

“ዓለም አቀፉ የስደተኞች ቀን”፣ ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. “ተስፋ ከቤት ወዲያ” በሚል መሪ ቃል ታስቦ ውሏል።

XS
SM
MD
LG