በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማሊያውያን በረቂቅ ሕገ መንግስት ላይ ድምጽ ሰጡ


ፎቶ ቪኦኤ (ሰኔ 18, 2023. / Photos፡ George Attino VOA Bambara)
ፎቶ ቪኦኤ (ሰኔ 18, 2023. / Photos፡ George Attino VOA Bambara)

ማሊያውያን ዛሬ በሥልጣን ላይ ባለው ሁንታ በተረቀቀው ሕገ መንግስት ላይ ድምጻቸውን ሲሰጡ ውለዋል። ሁንታው የረቂቅ ሕገ መንግስት ላይ ድምጽ እንዲስጥ ማድረጉ የወታደራዊ መሪውን በምርጫ የመወዳደር ፍላጎት ያሳያል ሲሉ ተንታኞች በመናገር ላይ ናቸው።
በማሊ የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ቀውስ አንዲሁም የጂሃዲስቶች ጥቃት ለዓመታት መቀጠሉን ተከትሎ፣ ከሦስት ዓመታት በፊት ወታደራዊ ሁንታ ሥልጣኑን ይዟል።
የሁንታው መሪ ኮሎኔል አሲሚ ጎይታ በመጪው ዓመት አገሪቱን ወደ ሲቪል አስተዳደር ለማሸጋገር ቃል ገብተዋል። 8.4 ሚሊዮን ማሊውያን በረቂቅ ሕገ መንግስቱ ላይ ድምጽ ለመስጠት መብታ አላቸው ተብሏል።
ኮሎኔል አሲሚ ጎይታ በባማኮ በቅድሚያ ድምጽ ከሰጡት አንዱ ሲሆኑ፣ በመዲናዋ በርካቶች ወደ ምርጫ ጣቢያ ሲያመሩ መታየታቸውን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG