በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራቅ ያዚዲዎች ወደ ትውልድ ቦታቸው በመመለሥ ላይ ናቸው


የያዚዲ ማሕበረሰብ አባላት አዲስ ዓመታቸውን ሲያከብሩ (ፎቶ ፋይል ሮይተርስ ሚያዚያ 19፣ 2023)
የያዚዲ ማሕበረሰብ አባላት አዲስ ዓመታቸውን ሲያከብሩ (ፎቶ ፋይል ሮይተርስ ሚያዚያ 19፣ 2023)

ከዘጠኝ ዓመታት በፊት በእስላማዊ ስቴት አሸባሪዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው የነበሩትና ያዚዲ በመባል የሚታወቁት የኢራቅ እዳጣን ማሕበረሰብ አባላት ወደ ትውልድ ቦታቸው በመመለስ ላይ ናቸው።

የቪኦኤው ካዋ ኦመር ከኢራቅ ከላከው ዘገባ መረዳት እንደተቻለው፣ መንግስት መኖሪያ እንደሚገነባላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል። አለማቀፉ የስደት ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ርዳታ በማድረግ ላይ እንደሆነም ታውቋል።

መገለልና በደል ይደረስባቸው የነበሩትና የኩርዲሽ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑት የያዚዲ ማሕበረሰብ አባላት እንደሚናገሩት፣ ለመመለስ መወሰናቸውን በመመልከት መንግስት እና ዓለም አቀፍ ርዳታ ለጋሾች ድጋፍ እንደሚያደርጉላቸው ተስፋቸውን ተናግረዋል።

በእ.አ.አ 2014 የኢስላሚክ ስቴት ሽብር ቡድን ከተማቸውን ሲያጠቃ፣ መኖሪያቸውን ለቀው ለመሄድ ተገደው ነበር። የሽብር ቡድኑ በአሁኑ ወቅት የሚቆጣጠረው ቦታ ባይኖርም፣ በሲቪሎች እና በጸጥታ ኃይሎች ላይ አልፎ አልፎ ጥቃት በመሠንዘር ላይ ነው።

በሺሕ የሚቆጠሩ የዚዲ ማሕበረሰብ አባላት ኩርዲስታን ተብሎ በሚጠራው ክልል አሁንም በመጠለያ መንደሮች ውስጥ እንደሚኖሩ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG