በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማሊ የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል ከግዛቷ እንዲወጣ እንደምትሻ አስታወቀች


የማሊ ካርታ
የማሊ ካርታ

የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱላዬ ዲዮፕ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ከሀገራቸው በአስቸኳይ እንዲወጣ በትናንትናው ዕለት አሳሰቡ።

ዲዮፕ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ፣በማሊ የሚገኘውን ሁለገብ የተቀናጀ የጸጥታ ማስፈን ተልዕኮ በምህጻሩ ሚኑስማ ኃይል በአስቸኳይ ከስምሪት እንዲነሳ እንደሚሹ ተናግረዋል ።

"ሚኑስማ በማሊ ሰላም፣ ዕርቅ እና ብሄራዊ ትስስር ላይ ከፍተኛ ጉዳት በሚያደርሱ ውንጀላዎቹ አማካይነት ማህበረሰባዊ ውጥረትን በማባባስ የችግሩ አካል የሆነ ይመስላል" ብለዋል ሚኒስትሩ።

"ይህ ሁኔታ በማሊ ህዝቦች መካከል እንዲሁም በማሊ ባለስልጣናት እና በሚኒሱማ መካከል ያለመታማመን ቀውስ እየፈጠረ ነው" ሲሉ ዲዮፕ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል።

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ማሊ ከጎረጎሳዊያኑ 2012 ጀምሮ የታጣቂዎችን ጥቃት በመጋፈጥ ላይ ትገኛለች ። የተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ከአውሮፓዊያኑ 2013 ጀምሮ በሀገሪቱ ቢሰማራም መረጋጋትን ማስፈን ግን አልቻለም

XS
SM
MD
LG