በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩጋንዳ ውስጥ በትምህርት ቤት ላይ በደረሰ ጥቃት በትንሹ 40 ሰዎች ተገደሉ


የዩጋንዳ ካርታ
የዩጋንዳ ካርታ

በምዕራብ ዩጋንዳ በሚገኝ ትምህርት ቤት ላይ በደረሰ የሽብር ጥቃት በትንሹ 40 ሰዎች መገደላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው "ምፖንድዌ" በተሰኘ ስፍራ "ሉቢሪራ" ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ከ ኢስላሚክ ስቴት ቡድን ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት ከተገደሉት በተጨማሪ ቢያንስ ስምንት ሰዎች መቁሰላቸውን ፖሊስ ገልጿል።

ከተጎጂዎች መካከል ምን ያህሉ ህጻናት እንደሆኑ እስካሁን አልተገለጸም።
ወታደሮች ወደ ቫይሩንጋ ብሔራዊ ፓርክ የሸሹትን አጥቂዎች በማሳደድ ላይ እንደሚገኙ ተዘግቧል ።

XS
SM
MD
LG