በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትምህርት የተቡ እና የሰሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የማበርታት አነቃቂ መሰናዶ


በትምህርት የተቡ እና የሰሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የማበርታት አነቃቂ መሰናዶ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:45 0:00

በዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ዘርፈ ብዙ ጫናዎችንና ሒደቶችን አልፈው የተመረቁ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ያከበረ እና ያበረታ ዝግጅት፣ ከሰሞኑ በቨርጂኒያ ግዛት ተከናውኗል።

የአክብሮት እና የማበርታት ዝግጅቱ ወጣኒ እና ፈጻሚ፣ “ሜዳ ኮፌ እና ኪችን” የተሰኘው ድርጅት ሲኾን፣ የድርጅቱ ባለቤቶች፣ ዝግጅቱ፥ በትምህርት ዓለም የበረቱትን ትውልደ ኢትዮጵያውያን የበለጠ ለማጠናከር፣ ተተኪዎችን ደግሞ ለማነቃቃት እንደተሰናዳ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል ።

በዝግጅቱ እንደቀረበው፣ ተመራቂዎች ወደ ገሃዱ የሥራ ዓለም ሲገቡ፣ እንዲያጤኗቸው ስለሚያስፈልጉ ጉዳዮች እና ለሥራ ብቁ ሊያደርጓቸው በሚችሉ ተጨባጭ ክህሎቶች ዙሪያ፣ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ በየሥራ መስካቸው ስኬታማ የኾኑ ተጋባዥ ተናጋሪዎች፣ የማነቃቂያ ንግግር እና የሕይወት ዓለም ምክር ለግሰዋል።

ሀብታሙ ሥዩም ከአዘጋጆቹ እና ከዝግጅቱ ተሳታፊዎች ጋራ ያደረገው ቆይታ ከሥር ተያይዟል።

XS
SM
MD
LG